በኢትዮጵያ ደቡባዊና ምሥራቃዊ አካባቢዎች እንዲሁም በጎረቤት ሶማሊያና ኬንያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል። እ.ኤ.አ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 2025 ሊዘንብ ይገባ የነበረው ዝናብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመክሸፉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ የምግብ እጥረትና ለኑሮ መቃወስ ተጋልጠዋል። በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ምሥራቃዊ ክፍሎች፣ እንዲሁም እንደ ቦረና እና ባሌ ያሉ አካባቢዎች ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ተከታታይ […]