የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል ሲሰራበት የቆየውንና ኋላ ቀር የሆነውን የእፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን አዋጅ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። ይህ አዲስ የጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1400/2018 ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም የሥነ ሕይወት ዕፅዋት ብልሽትንና ብክነትን መከላከል እንዲሁም ዘመናዊ የተባይ መከላከልና መቆጣጠር […]