የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የዳሽን ባንክን አክሲዮኖች መዘገበ

ዳሸን ባንክ አዲስ እየተገነባ ባለው የካፒታል ገበያ ሥርዓት ውስጥ ታሪካዊ ስፍራ ይዟል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ከ14.3 ሚሊዮን በላይ ነባር መደበኛ አክሲዮኖች እና 2.2 ሚሊዮን አዳዲስ አክሲዮኖች እንዲመዘገቡ ፈቅዷል። ይህ ምዝገባ ባንኩ ወደፊት ለሚያካሂደው የነባር አክሲዮኖች ሽያጭ (Rights Issue) እና በኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች (ESX) ላይ ለሚኖረው […]