ስንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ በ480 ሚሊዮን ብር የተመዘገበ ካፒታል ይዞ በይፋ ሥራ ጀምሯል። ባንኩ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሥራ ፈቃድ ዛሬ ያገኘ ሲሆን፣ ይህም በዘርፉ ከተሰማሩ አምስት ተቋማት መካከል በካፒታል መጠኑ ግዙፉ ያደርገዋል። ይህ አዲስ የኢንቨስትመንት ባንክ በስንቄ ግሩፕ ስር የተቋቋመ ሦስተኛው ድርጅት ሲሆን፣ የባንኩ ፕሬዝዳንት ነዋይ መገርሳ እንደገለጹት አራተኛው እህት ኩባንያም በመመሥረት ላይ ይገኛል። አዲሱን […]