በአለም አቀፍ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ግዙፍ ስም ያለው ካርፎር፣ ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የኩዊንስ ሱፐርማርኬትን ተክቶ ስራ ሊጀምር ነው። በጀማል አህመድ የሚመራው የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በስራ ላይ የሚገኙትን 13 የኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች በሙሉ ወደ ካርፎር የንግድ ምልክት ለመቀየር ተስማምቷል። የሽግግሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በጎርጎሮሳውያን ዘመን እስከ 2026 አጋማሽ ድረስ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ […]