የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም ላይ አራተኛውን ግምገማ በማጠናቀቁ፤ አገሪቱ የ261 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንድታገኝ መወሰኑን አስታወቀ። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ በፕሮግራሙ ሥር እስካሁን ያገኘችውን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ወደ 2.183 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያደረገው ሲሆን፣ ገንዘቡ አገሪቱ የውጭ ክፍያ ሚዛንና የበጀት ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታል። የድርጅቱ […]